የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ከ26 ሺሕ በላይ ሕገ ወጥ የጦር መሳርያዎችን አስወገደ

መጋቢት 2/2014 (ዋልታ) በደቡብ አፍሪካ የጋውቴንግ ፖሊስ ከ26 ሺሕ በላይ ሕገ ወጥ የጦር መሳርያዎች ማስወገዱን አስታወቀ።

ጋውቴንግ በደቡብ አፍሪካ ሀብታም ከሚባሉና የተለያዩ ህገወጥ ድርጊቶች ከሚፈጸሙባቸው ግዛቶች አንዷ መሆኗን መረጃዎች ያሳያሉ።

የግዛቷ ፖሊስ ቃል አቀባይ ኮሎኔል አትህሌንዳ ማትህ ሕገ ወጥና ፍቃድ የሌላቸው መሳርያዎችን ለመቆጣጠር እንዲሁም ወንጀልን ለመከላከል ዘመቻ ተካሂዷል ብለዋል።

በዘመቻውም ፖሊስ ከ26 ሺሕ በላይ የጦር መሳርያዎች ማስወገዱን አስታውቀው የተወገዱት የጦር መሳርያዎች ለወንጀል ድርጊት መዋላቸው ላይ ምርመራ ተደርጎባቸዋል ነው ያሉት።

አብዛኛዎቹ የተወገዱት መሳርያዎች በፖሊስ ፍተሻ የተያዙና በፍቃደኝነት የተሰጡ መሆናቸውንም ዘ ሳውዝ አፍሪካን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

የደቡብ አፍሪካ ጎዳናዎች ሰላማዊነታቸው እስከሚረጋገጥ ድረስ የሚያካሂደው ዘመቻ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል።