የደቡብ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ተጀመረ


ሐምሌ 26/2013 (ዋልታ) –  
የደቡብ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አምስተኛ ዙር ስድስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተጀመረ።

ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ጉባዔው በተለያዩ አጀንዳዎች ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ተመልክቷል።

በዛሬ ውሎው የክልሉ መንግሥት የ2014 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድና በጀት ከያዛቸው አጀንዳዎች መካከል ናቸው ።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋናው ኦዲት መሥሪያ ቤት የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2014 የስራ ዘመን ጠቋሚ ዕቅድ ላይ እንደሚወያይም ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ የጌዴኦ ባህላዊ መልከአ ምድር ቅርሶችን ለመጠበቅ የወጣን ጨምሮ የተለያዩ ረቂቅ ዓዋጆች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅና ሹመት እንደሚኖርም የጉባዔው መርሃ ግብር ያሳያል።