የደቡብ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር መስራች ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

መስከረም 22/2014 (ዋልታ) 6ኛው ዙር የደቡብ ብሄሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባኤ መካሄድ ጀመረ፡፡

በጉባኤው የአዲሱን ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች፣ ርዕሰ መስተዳደር እና የክልሉን መንግስት የካቢኔ አባላት ይሰየማሉ፡፡

የክልሉን አስፈጻሚ አካላት ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣውን ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ማጽደቅ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትን መወከል የእለቱ አጀንዳዎች እንደሚሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በሰለሞን በየነ