የደቡብ ክልል በኦሮሚያ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች 20 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

የካቲት 7/2014 (ዋልታ) የደቡብ ክልል በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል 20 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉን የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው ለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ያስረከቡ ሲሆን ድጋፉ በክልሉ ቦረና እና ጉጂ ዞኖች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚውሉ የተለያዩ ምግብ ነክ ቁሳቁስን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ድጋፉ በአካባቢዎቹ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው እንስሳት የሚውል መኖ ያካተተ መሆኑን ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡