የደቡብ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የጤፍ ማሳ ጉብኝት

ጳጉሜ 02/2013 (ዋልታ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ በክላስተር እየለማ ያለ የጤፍ ማሳን ዛሬ ጎብኝተዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ እና በእርሳቸው የተመራው ልኡክ በሌሎችም የክልሉ አካባቢዎች በመዘዋወር የመኸር ሰብሎችን እንደሚጎበኙ ከክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።