የደቡብ ክልል የበልግ ልማት ንቅናቄ በቡታጅራ እየተካሄደ ነው

መጋቢት 7/2014 (ዋልታ) የደቡብ ክልል የ2014 ዓ.ም የበልግ ወቅት የግብርና ልማት የንቅናቄ መድረክ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው በተገኙበት በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የክልሉ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አፈጻጸምና በቀጣይ ጊዜያት በሰፊው የሚካሄደው የበልግ ወቅት ልማት ቅድመ ዝግጅት በዝርዝር እንደሚገመገም ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡