የደቡብ ክልል የክረምት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃግብር ተጀመረ

ሐምሌ 01/2013 (ዋልታ) – የክረምት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መረሃ ግብር በክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳደር በአቶ እርስቱ ይርዳው በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።

የክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳደር  አቶ እርስቱ ይርዳው  በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ በቦኢቴ ቀበሌ በመገኘት የአቅመ ደካሞችን ቤት የማስጠገን ስራ አካሂደዋል።

በክልሉ በሚካሄደው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ከ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ  የገለፁት ርዕስ መስተዳደሩ  በክረምት ከሚከናወኑ ተግባራቶች በዋናነት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ፤ የአቅመ ደካሞች ቤት ዕድሳትና የከተማ ጽዳት በገጠርና በከተማ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

በመረሃ ግብሩ የክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳደር፣ የክልሉ ብልጽግና ፖርቲ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፤ ፣ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ አስቴር ከፍታው እንዲሁም የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ሽፈራዉ ቦጋለ ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ ሃላፊዎች መገኘታቸውን  ከዴኦ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።