የደቡብ ዕዝ ለሠራዊቱ የሜዳይ ሽልማትና የማዕረግ ማልበስ ስነ ሥርዓት እያካሄደ ነው

ግንቦት 142014 (ዋልታ) በሀገር መከላከያ ሠራዊት የደቡብ ዕዝ 83ኛ ክፍለ ጦር የሜዳይ ሽልማት እና የማዕረግ ማልበስ ስነ ሥርዓት እያካሄደ ነው።

በስነ ሥርዓቱ ላይ የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋን ጨምሮ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተገኝተዋል።

የሜዳይ ሽልማትና የማዕረግ ዕድገት የሚሰጣቸው በሕልውና ዘመቻው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱና ጀብዱ ለፈፀሙ የሠራዊት አባላት መሆኑን የአሚኮ ዘገባ ያመለክታል።
የሜዳይ ሽልማቱና የማዕረግ እድገቱ ሠራዊቱ በቀጣይ ለሚኖረው ሀገራዊ ግዳጅ የበለጠ መነሳሳት እንደሚፈጥርለት ይጠበቃል።