የደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማእከል የተዋጊ መሃንዲስ ሙያተኞችን አስመረቀ

ሚያዝያ 2/2014 (ዋልታ) የደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማእከል በዕዙ ሥር ከሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች ለተወጣጡ የተዋጊ መሃንዲስ ሙያተኞችን አስመርቋል።

የማዕከሉ ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሎኔል ሁሴን አስረስ በሥልጠና ቆይታቸው የላቀ ውጤት ላመጡ ተመራቂዎች የተዘጋጀላቸውን ሽልማት አበርክተዋል።

ኮሎኔል ሁሴን አስረስ “በሀገራችን ላይ ሊቃጡ የሚችሉ ማንኛውም አይነት ጥቃት ለመመከት በውጊያ ምህንድስና ጥበብ ብቁ የኾኑ ተዋጊ የመሃንዲስ ሙያተኞች ማፍራት ያስፈልጋል” ብለዋል።

ተመራቂ ሙያተኞች ዓለም ከደረሰበት ውስብስብ የውጊያ ጥበብ አንፃር ራሳችሁን በየጊዜው ማብቃት እና የሚሰጣችሁን ማንኛውም ግዳጅ ሙያው በሚጠይቀው ክህሎት እና አስተሳሰብ መወጣት ይገባችኋል ሲሉ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ አመላክቷል።