የደባርቅና የአካባቢው ተወላጆች ከ1.6 ሚሊየን ብር ለሠራዊቱ የእርድ ሰንጋዎችን አቀረቡ

የእርድ ሰንጋዎች

ነሐሴ 24/2013 (ዋልታ) – በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የደባርቅ እና የአካባቢው ተወላጆች ከ1.6 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊት የእርድ ሰንጋዎችን አቅርበዋል።

ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ያቋቋሙት ዋልያ በጎ አድራጎት ማህበር በአሸባሪው ቡድን  አማካኝነት ተፈናቅለው በሰሜን  ጎንደር ዞን በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ  ዜጎችን  ለመደገፍ  እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

ማህበሩ የተጀመረው ህልውናን የማስከበር ዘመቻ እስኪጠናቀቅ ለሰራዊቱ የሚያደርገውን ድጋፍ  እንደሚቀጥልም ተገልጿል።

ድጋፉን  የተረከቡት  የደባርቅ  ከተማ  ከንቲባ  አቶ  ሰለሞን  ተዘራ  የደባርቅ  ከተማ አስተዳደር የሎጅስቲክ አቅርቦት ከማስተባበር ባለፈ በዞኑ ከ4ሺህ በላይ ወጣቶች  በመሠረታዊ  ውትድርና  ሰልጥነው  ግንባር  እንዲሰለፉ እንደተደረገ ገልጸዋል።

(በታሪኳ መንገስተዓብ)