የደብረ ማርቆሱ እቴ ግራናይት ፋብሪካ የሙከራ ምርት ጀመረ

ጥር 29/2014 (ዋልታ) በደብረ ማርቆስ ከተማ የተገነባው እቴ የግራናይት ፋብሪካ የሙከራ ምርት ጀመረ።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በአያልነህ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተገነባው እቴ የግራናይት ፋብሪካ 360 ሚሊዮን ብር ወጭ እንደተደረገበት የአሚኮ ዘገባ ጠቅሷል።