የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ለኅልውና ዘመቻ የሚውል ከ57 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ፡፡

ጥቅምት 17/2014 (ዋልታ) የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ለኅልውና ዘመቻ የሚውል ከ57 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ፡፡
የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አካሉ ወንድሙ ከመንግሥት ሰራተኞች 32 ሚሊዮን 849 ሺሕ ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል አሳውቀዋል፡፡
በተጨማሪም ከንግዱ ማኅበረሰብ 19 ሚሊዮን፣ ከከተማው ነዋሪ 4 ሚሊዮን እንዲሁም ከአርሶ አደሮች 364 ሺሕ 380 ብር መሰብሰቡን አክለዋል፡፡
የአስተዳደሩ መረጃ እንደሚጠቁመው የከተማዋ ነዋሪዎች ለኅልውና ዘመቻው የሚያደረጉትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል፡፡