የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት የማኅበራዊ ተፅዕኖዎች ቅነሳ መስፈርት መሰረት እየተተገበረ ነው

የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት

ሚያዝያ 3/2014 (ዋልታ) የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት የዓለም ባንክ ባስቀመጠው የአካባቢ እና ማኅበራዊ ተፅዕኖዎች ቅነሳ መስፈርት መሰረት እየተተገበረ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በፕሮጀክቱ አተገባበር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው።

መድረኩ ፕርጀክቱ ሲተገበር የሚፈጠሩ የአካባቢ እና ማኅበራዊ ተፅዕኖዎችን ለመቀነስ የሚያስችሉ መሳሪያዎች አስፈላጊነትና አጠቃቀም፣ በአፈፃፀም ወቅት የሚፈጠሩ ቅሬታዎች እና የአፈታት ሥርዓት ላይ በቂ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነው ተብሏል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ መድረኩ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማን በተሻለ ሁኔታ ለማሳካትና የፕሮጀክቱን ትግበራና አፈፃፀምን ለማሻሻል ያግዛል ብለዋል።

በሚኒስቴሩ የሚመራው የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት ውስጥ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት መካተታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW