መስከረም 19/2014 (ዋልታ) አዲሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ከሰዓት ባካሄደው 3ኛ የስራ ዘመን የመጀመሪያ ዓመት 49ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ያቀረቧቸውን ሹመቶች አፅድቀዋል።
የተሾሙ የካቢኒ አባላትም የሚከተሉት ናቸው፡-
- ሀርቢ ቡህ ወርሰሜ – ም/ከንቲባና ንግድ ቢሮ ሃላፊ
- ኢብራሂም ዩሱፍ – የመንግስት ተጠሪ
- ሱልጣን አሊይ – ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ
- ሮቤል ጌታቸው – ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ሃላፊ
- ኑረዲን አብደላ – ግብርና ቢሮ ሃላፊ
- ጀማል ኢብራሂም – ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ
- ለምለም በዛብህ – ጤና ጥበቃ ቢሮ ሃላፊ
- አብዱሰላም አህመድ – ፍትህ ቢሮ ሃላፊ
- ሳጂድ አሊይ ሁሴን – መሬት ልማት ቢሮ ሃላፊ
- ሙሉካ መሀመድ ሁሴን – ትምህርት ቢሮ ሃላፊ
- ኢስቂያስ ታፈሰ – መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ
- ፈጡም ሙስጠፋ ሀቢብ – ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ሃላፊ
- አቡበከር አዶሽ ኦልሀዬ – ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ
- ጫልቱ ሁሴን – ዋና ኦዲተር
- አብዱሰላም መይደኔ- ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር
መረጃውን ያገኘነው ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽ/ቤት ነው