የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለ16ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ

ከንቲባ ከድር ጁሀር

ኅዳር 22/2014 (ዋልታ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ኅዳር 29 የሚከበረውን 16ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ለማክበር በቂ ዝግጅት ማደረጓን ከንቲባ ከድር ጁሀር አስታወቁ።

የህብረ ብሔራዊ ብዝኃነት መገለጫ የሆነው የድሬዳዋና ዙሪያዋ ነዋሪዎች እንግዶቹን ለመቀብል ዝግጁ መሆናቸውንም ከድር ገልፀዋል።

“ወንድማማችነት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በስኬት ለማጠናቀቅ ከጤና እና የፀጥታ ጉዳዮች አንፃር አስተማማኝ ዝግጅት ተደርጓል ነው የተባለው።

ኢትዮጵያ በሽብርተኛው ሕወሓትና የውጭ ኃይሎች የኅልውና ፈተና ላይ ባለችበት ወቅት ወንድማማችነት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል መከበሩ የኢትዮጵያ ህዝቦች በደም የተሳሰረ ማንነት ያላቸው መሆኑን አመላካች መሆኑን ከንቲባው በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በበዓሉ ላይም ለአሀር መከላከያ ሰራዊት ደም የመለገስ፣ ለተፈናቃዮች እርዳታ የማድረግና ለዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ የማድረግ ተግባሮች እንደሚከናወኑ ይፋ ሆኗል።

በደምሰው በነበሩ