የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4.8 ቢሊየን ብር በጀት አፀደቀ


ሐምሌ 28/2013 (ዋልታ) –
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ የስራ ዘመን 47ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አጀንዳዎችን በማፅደቅ ተጠናቋል።
አስተዳደሩ የ2014 አመት አጠቃላይ በጀት ብር 4,882,482,131 ሆኖ የቀረበ ሲሆን የምክር ቤቱ ሰጥቶበት ጸድቋል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የ2013 ሪፖርትና የ2014 በጀት አመት እቅድ፣ የመሬት ምዝገባ ጽ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ፣ የ2013 ተጨማሪ በጀት ውይይት ተደርጎበት ጸድቋል፡፡
ምክር ቤቱ በ47ኛ መደበኛ ጉባኤው አቶ ሰሚር ረሺድን የድሬዳዋ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ አድርጎ ሾሟል፡፡
የምክር ቤቱ አባላትም በነገው እለት በአስተዳደሩ በአራቱም ክላስተሮችና 9 የከተማ ቀበሌዎች በሚደረገው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በየአካባቢያቸው ተሳታፊ እንደሚሆኑ ከአስተዳዱ ከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡