የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 3 ሺሕ 559 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ

ጥቅምት 27/2014 (ዋልታ) የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ13ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3 ሺሕ 559 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ነው፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 1 ሺሕ 6 ተማሪዎች ሴቶች መሆናቸው ተጠቁሟል።

ዩኒቨርሲቲው የሚያስመርቃቸው በመደበኛና ተከታታይ መርኃግብር ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያና በሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች መሆናቸውም ተመላክቷል።

በመማር ይበልጣል (ከድሬዳዋ)