የዶ/ር አምባቸው መኮንን ፋውንዴሽን ምስረታ ይፋ ሆነ

በፋውንዴሽኑ የምስረታ ዝግጅት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤና አክቲቪስት ታማኝ በየነ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በከተማ መስተዳድሩ ስም በልደታ አካባቢ ለፋውንዴሽኑ የሚሆን የመስሪያ ቤት ቦታ እንዳበረከቱ ገልፀዋል።

የፋውንዴሽኑ ዋና አላማም ዶክተር አምባቸው በህይወት እያሉ የጀመሯቸውን ሊሰሯቸው የሚችሏቸውን ስራዎች ማስቀጠል እንደሆነ የዶክተር አምባቸው ልጅ መዓዛ አስታውቃለች።

ፋውንዴሽኑ በትምህርት፣ በጤና እና በአረንጓዴ ልማት ከሚሰራቸው ስራዎች በተጨማሪ እውነትንና ሀቀኝነትን ይዞ የአገርን ልማት የሚያግዝ ማህበረሰብ ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል።

(በደምሰው በነበሩ)