የጃፓን-አፍሪካ አጋርነት ፎረም እየተካሄደ ነው

ሚያዝያ 25/2014 (ዋልታ) ሁለተኛው የጃፓን-አፍሪካ የግልና የመንግሥት አጋርነት ፎረም በኬንያ-ናይሮቢ ከተማ ተጀምሯል።

በመድረኩም ኢትዮጵያ እየተሳተፈች ሲሆን የኢትዮጵያ እና የጃፓን የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት ይበልጥ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጃፓን 3ኛዋ የቡና ምርት ተቀባይ ሀገር ናት ብለዋል።

በቀጣይም ሌሎች የወጪ ምርቶችን ጭምር በዓይነትና በመጠን ለመጨመር የኢትዮጵያ ዝግጁነት አሳውቀዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW