የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ

ሰኔ 20/2013 (ዋልታ) – የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሃመድ በ750 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገነባውን የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ በይፋ አስጀመሩ፡፡

ፕሮጀክቱ  በቻይናው የሲቪል ስራ ኮንስትራክሽን ድርጅት የሚከናወን ሲሆን ግንባታው በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።

የፕሮጀክቱ ወጪ ሙሉ በሙሉ በሶማሌ ክልል የሚሸፈን ሲሆን ሲጠናቀቅ 264 ሺህ 356 የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የክልሉ ውሃ ቢሮ ሀላፊ  አብዱረህማን አህመድ ፕሮጀክቱ ላለፉት 10 አመታት ይሰራል ተብሎ የባከነ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ጅግጅጋ ከተማ በአሁኑ ወቅት 9 ሺህ 745 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃን በቀን የምታገኝ ሲሆን የፕሮጀክቱ መጠናቀቅ የከተማዋን የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋን እንደሚያሳድግ ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡