የገቢዎች ቢሮ 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የዓይነት ድጋፍ አደረገ

ታኅሣሥ 17/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች አሸባሪው የትሕነግ ወራሪ ኃይል በከፈተው ጦርነት ጉደት ለደረሰባቸው ወገኖች 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የዓይነት ድጋፍ አደረጉ።
የቢሮው የሕግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ኮማንደር አህመድ መሀመድና የሞደርናይዜሽንና ኮርፓሬት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ውዴ ቴሶ ብርድልብስ፣ ፍራሽ፣ ዘይት፣ መኮረኒ፣ ሩዝ የንፅህና መጠበቂያ፣ ፈሳሽ ሳሙና፣ የቤት ዕቃዎችና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለደሴ ከተማ ከንቲባ አበበ ገብረመስቀል አስረክበዋል።
ኃላፊዎቹ የቢሮዎ አመራሮችና ሰራተኞች ለአገር መከለከያ ሰራዊት የወር ደመወዛቸውን ከመስጠታቸውም ባሻገር በጦርነቱ ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ወገኖችም ካላቸው ላይ በማዋጣት ድጋፍ እያደረጉ ነው ብለዋል።
ከንቲባ አበበ ገብረመስቀል በዓይነት የተደረገልንን ድጋፍ ለሚገባቸው ሰዎች በትክክል እናደርሳለንም ብለዋል።
የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች 13 ነጥብ 5 ሚሊዮን በማሰባሰብ ከ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የዓይነት ድጋፍ ለደሴ ከተማ ያበረከቱ ሲሆን ሌላውን ደግሞ ለአፋር ክልል ተጎጂዎች ዛሬ ያበረክታሉ ተብሏል።
በምንይሉ ደስይበለው (ከደሴ)