የጊኒ ቢሳው ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

የካቲት 9/2015 (ዋልታ) የጊኒ ቢሳው ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዝዳንቱ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው የሥራ ቆይታ የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የ50 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ ከሁለት ዓመት በፊት በጊኒ ቢሳው የተካሄደውን ምርጫ አሸንፈው ሀገሪቱን በመምራት ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

በደረሰ አማረ