መስከረም 20/2014 (ዋልታ) – የጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት መስራች ጉባዔ አቶ ኡሞድ ኡጁሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድረጎ መረጠ።
አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
ጉባዔው ወ/ሮ ባንቺአየሁ ዲንገታን ዋና አፈጉባዔ እንዲሁም ወ/ሮ ትሁት ሀዋሪያትን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ መምረጡ ይታወቃል።
ኢብኮ እንደዘገበው መስራች ጉባዔው ክልሉን በቀጣይ የሚያገለግሉ የካቢኔ አባላትና ሌሎች ሹመቶችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።