የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 1 ሺህ 229 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።
በመጀመሪያ ዲግሪ 958 ተማሪዎችን የሚመረቁ ሲሆን፣ 389 ሴቶችና 596 ወንዶች ናቸው።
በሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ 45 ተማሪዎች የሚመረቁ ሲሆን፣ ከነዚህ መካከል አምስቱ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌን ጨምሮ ሌሎች በርካታ እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።