መጋቢት 28/2014 (ዋልታ) የሚኒስትሮች የጋራ ግብር ሃይል እስካሁን የተካሄዱ የምርመራና የመልሶ ማቋቋም ሥራን እየገመገመ ነው።
የሰሜኑን ግጭት ተከትሎ በአማራ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች የተፈፀሙ ወንጀሎችን እንዲሁም የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ምን እንደሚመስሉ እና ያሉበትን ደረጃ ተመልክቷል።
በተለይም ሥራውን በጀመረባቸው በአማራና አፋር ክልሎች የተፈፀሙ ወንጀሎችን የማጣራትና ወንጀለኞቹን ለፍርድ የማቅረብ ሂደት ያለበት ደረጃ በዝርዝር ታይቷል።
እስካሁን ወንጀሎች እና ወንጀሎቹ በማንና እንዴት ተፈፀሙ ከሚለው ጋር በተገናኘ በርካታ የአይን ምስክሮችን ለማነጋገር መቻሉን እና በቂ ማስረጃ በማሰባሰብ ወንጀለኞች ላይ ክስ ለመመስረት ሂደት መጀመሩ ተገልጿል። በሂደቱ የተገኙ ስኬቶችና እጥረቶችም መዳሰሳቸወን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡