የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ቻይና ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች

የካቲት 20/2015 (ዋልታ) በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ቻይና ድጋፍ እንደምታደርግ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዚዩዋን ገለጹ።

በግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዚዩዋን ጋር የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ማሳደግ በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዚዩዋን በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና ምርታማነትን ለማሳደግ በዘርፉ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ላይ ቻይና ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎች እና ቴክኖሎጂዎች ላይ ቻይና ድጋፍ እንደምታደርግም አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እና ምርታማነትን ለማሳደግ በዘርፉ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎች እና ቴክኖሎጂዎች ላይ ቻይና ደግፍ እንደምታደርግ አምባሳደሩ በውይይታቸው አንስተዋል፡፡

በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ ላይ ተሰማርተው እንዲሰሩ የሚያችል ስራ እንደሚሰራ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።