የግብርና ባለሙያዎች በፊንፊኔ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አደረጉ

የካቲት 14/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ልዩ ዞን ፊንፊኔ ዙሪያ የመስኖ ስንዴ ልማት ጉብኝት እና የአርሶ አደሮች ልምድ ልውውጥ ተደረገ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ አዘጋጅነት በሰበታ አዋሽ ወረዳ የሚገኙ ቀበሌዎች ውስጥ የመስኖ ስንዴ ልማትን በመጎብኘት የጉጂ ዞን አርሶ አደሮችና ባለሙያዎች የልምድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡

የልምድ ልውውጡ አርሶ አደሮቹ ከሞዴል አርሶአደሮች ጥሩ ልምድ እንዲያገኙና በኑሯቸው ራሳቸውን ችለው እንዲኖሩ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡

አስቴር ጌታሁን