ሚያዝያ 19/2013 (ዋልታ) – የጎርጎራና አካባቢው ያለውን የኢኮ ቱሪዝም ሀብት ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታወቀ።
የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሽ ግርማ እንደገለፁት፤ ጎርጎራና አካባቢው የውሃ ተኮር ቱሪዝምና የባህልና ታሪክ ተኮር ቱሪዝም ብቻ ሳይሆን ሁለቱንም ያጣመረ የተፈጥሮ ሀብቱን የጠበቀ የቱሪዝም ባለቤት ነው።
” ጎርጎራ በልዩ ሁኔታ ለኢኮ ቱሪዝም ትልቅ አበርክቶት ያላት ስፍራ ናት፤ ይህ አይነቱ የቱሪዝም ዘርፍ የአካባቢን ምርት በመጠቀም ቱሪስቶችና ማህበረሰቡን የእርስ በርስ ግንኙነት በማጠናከር ትልቅ ገቢ ያስገኛል፤ የሥራ ዕድል በስፋት ይፈጥራልም ” ብለዋል።
ባህር ዳር አካባቢ ውሃ ተኮር የቱሪዝም ሀብት በስፋት እንዳለና ጎንደር አካባቢ ደግሞ ታሪካዊና ባህላዊው የሆነ የቱሪዝም መስህብ መኖሩን የገለጹት አቶ ስለሽ፣ ጎርጎራ ከሁለቱም በተለየ መንገድ የኢኮ ቱሪዝም ሀብት በስፋት ያለው መሆኑን ጠቁመዋል።
በተለይ በውሰጡ ዓሣና ጉማሬ ያለው ሐይቅ መኖሩ ሌላ የቱሪስት መስህብ መሆኑንም አንስተዋል።
በአካባቢው እራሱን የቻለ የቱሪስት መስህብ መሆን የሚችል ብዛት ያለው የወፍ ዝርያ እንደሚገኝና በሃይቁ አካባቢ ፍራፍሬ፣ ልዩ ልዩ የግብርና ምርቶች ይገኙበታል ብለዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/waltainfo
የአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/%D8%AA%D9%84%D9%81%D8%B2%D9%8A%D9%88%D9%86-%D9%88%D8%A7%D9%84%D8%AA%D8%A7-%D8%A8%D8%A7%D9%84%D8%B9%D8%B1%D8%A8%D9%8A-Walta-TV-Arabic-102134881551994/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!