የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለ35 ህፃናት የበዓል ስጦታ አበረከተ

ታኅሣሥ 23/2014 (ዋልታ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ35 ህፃናት ስጦታ አበረከተ።

ጽሕፈት ቤቱ እነዚህን ህፃናት በቋሚነት በማገዝ እንደሚያሳድጋቸውም ተገልጿል።

ስጦታው የተበረከተላቸውና በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ስር የሚታገዙት ህፃናት እያንዳንዳቸው የትምህርት ቁሳቁስ፣ የምግብና የአልባሳት ድጋፍን ጨምሮ የ1 ሺሕ ብር ስጦታ እንደተበረከተላቸው ኢብኮ ዘግቧል።

መርሐግብሩ ህፃናት ከቤተሰቦቻቸው ሳይነጠሉ ባሉበት ሆነው እንዲደገፉና ወደ ጎዳና ህይወት የሚገፏቸውን ችግሮች መቀነስን ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር በመሆን 320 ህፃናትን እየደገፉ ይገኛሉ ተብሏል።

ሌሎች የግል ተቋማትና ግለሰቦች በተመሳሳይ ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ህፃናትን እያሳደጉ ይገኛሉ፡፡