የጠ/ሚ/ር ዐቢይ አብረን እንስራ ጥሪ

ጳጉሜ 4/2013 (ዋልታ)   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጋራ ለመስራት ከቆረጥን አፍሪካ ያላት የተፈጥሮና የሰው ሃብት ወደታላቅነት ለመጓዝ በቂያችን በመሆኑ አብረን እንስራ ሲሉ ለአፍሪካዊያን ጥሪ አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ መሪዎችን ጠቅሰው ባስተላለፉት የቲውተር መልዕክታቸው የአፍሪካ ትብብር የአኅጉራችን እድገት መሰረት ነው ብለዋል፡፡

‹‹የአፍሪካ ጊዜ አሁን ነው›› ሲሉም ከሳምንት በፊት ያቀረቡትን የትብብር ጥሪ ደግመው አቅርበዋል፡፡