የጠ/ሚ/ር ዐቢይ ውሳኔ ሕዝቡ የአገሩን ሉአላዊነት ለማስከበር በወኔ እንዲነሳ ማድረጉ ተገለጸ

ኅዳር 16/2014 (ዋልታ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ግንባር የመዝመት ውሳኔ ሕዝቡ የአገሩን ሉዓላዊነት ለማስከበር በወኔ እንዲነሳ ማድረጉን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ ገለጹ፡፡

የአሸባሪው ሕወሓት አገርን የማፍረስና እንደ ሕዝብ የመጥፋት አደጋ ተደቅኖብናል የሚለውን ሀሳብ ለመረዳትና ለመዝመት እድል ሰጥቷል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

ኃላፊው በአማራ ክልል ወረራውን ለመቀልበስ የሁሉም ፓርቲ አመራር ወኪሎች ባሉበት በጋራ በጉዳዩ ላይ ዘመቻውን የሚመራ ኮሚቴ መቋቋሙን ተናግረዋል፡፡

ኮሚቴው እስከ ታች ድረስ መዋቅሩን በመዘርጋት የሎጂስቲክ አቅርቦቱንና ዘመቻውን በተቀናጀ ንቅናቄ እየተመራ መሆኑን አመልክተዋል።