የጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማት ድጋፍ

ነሐሴ 29/2013 (ዋልታ) – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እና ተጠሪ ተቋማት የሕወሓት የሽብር ቡድን በከፈተው ጥቃት ከአካባቢዎችና ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ፡፡
የሽብር ቡድኑ በከፈተው ጥቃት በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተጠልለው ለሚገኙ ወገኖች ነው የእለት ደራሽ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ያደረጉት፡፡
በመጠለያዎችም ነፍሰጡርና አራስ ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሴቶች፣ ህፃናትና አቅመ ደካሞች የሚገኙ ሲሆን በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን መደገፍ አስፈላጊ በመሆኑ ዜጎች ለዚህ በጎ ተግባር ሊረባረቡ እንደሚገባም ተቋማት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ተጠሪ ተቋማቱ በደቡብ ወሎ ዞን ወረዳዎች የአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት ማስጀመራቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
በእነዚህ አካባቢዎች በተቋማቱ ብቻ ከ10 በላይ ቤቶች እድሳት ለማከናወን መታቀዱም ተገልጿል፡፡