የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ሴኔጋል መግባት

ጳጉሜ 02/2013 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ሴኔጋል ዳካር ገብተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሴኔጋል ቆይታቸው ከሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ጋር የሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚያደርጉ እንደሚጠበቅ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡