የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ንግግሮችና መልዕክቶች የያዘ ከ”መስከረም እስከ መስከረም” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

ግንቦት 12/2016 (አዲስ ዋልታ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንግግሮችና መልዕክቶች የያዘ ከ”መስከረም እስከ መስከረም” የተሰኘ መጽሃፍ ለንባብ በቃ።

መጽሐፉ ላይም ሙያዊ ውይይት በወዳጅነት ፓርክ ተካሂዷል።

በመደረኩም ተማሪዎች ከመጽሐፉ የተመረጡ ገጾችን ለውይይት መነሻ ሃሳብ እንዲሆኑ በንባብ ያቀረቡ ሲሆን በተለያዩ የስራ መስኮች የተሰማሩ ተሳታፊዎችም በመጽሐፉ የተሰነዱ መልዕክቶች ላይ ሙያዊ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ከ”መስከረም እስከ መስከረም” የተሰኘው መጽሐፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ ሀገር አቀፍ ሁነቶች፣ ዓለም አቀፉ ጉባኤዎችና በዓላት ላይ ያስተላለፏቸውን 91 መልዕክቶችና ንግግሮች የያዘ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።