የጤናውን ዘርፍ ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

ጥር 25/2014 (ዋልታ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ  በጤናው ዘርፍ የሚደረገውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት ማካሄዳቸው ተገለጸ፡፡

በውይይታቸውም አገራቱ በጤናው ዘርፍ የሚያደርጉትን ትብብር ለማጠናከር እና  በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ላይ በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ሚኒስትሯ ጣሊያን በጤናው ዘርፍ ለኢትዮጵያ ለምታደርገው ያላሰለሰ ሙያዊ ድጋፍ  ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ  በበኩላቸው ኢትዮጵያ እና ጣሊያ ን በጤናው ዘርፍ ያላቸው ትብብር ተጠናክሮ  እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

ጣሊያን  በኮቪድ-19 ላይ የምታደርገውን ድጋፍም አጠናክራ እንደምትቀጥል አምባሳደሩ ማረጋገጣቸውን በኢትዮጵያ ከጣሊያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡