የጤና ሚኒስቴር ለአገር መከላከያ ሰራዊት 30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ኅዳር 17/2014 (ዋልታ) የጤና ሚኒስቴር አገርን ለመታደግ በግንባር እየተዋጋ ለሚገኘው የአገር መከላከያ ሰራዊት የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።
ሚኒስቴሩ በተጨማሪም 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፋን ያበረከቱት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ኢትዮጵያን ለመውረር የሚደረጉ የጠላት ሙከራዎች የመጀመርያ ጊዜ እንዳልሆነ ገልፀው ኢትዮጵያን ለማዳን ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
አያይዘውም ለአገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
በተመሳሳይ ዜና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ለሰራዊቱ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ያስረከቡት የኦሎምፒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ሰላም ከሌለ ስፖርት የለም ስለዚህ ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በዙፋን አምባቸው
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!