የፊቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ እየተከበረ ነው

የፊቼ ጫምባላላ በዓል

ሚያዝያ 21/2014 (ዋልታ) የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ ከተማ ሶሬሳ ጉዱማሌ እየተከበረ ነው።

የጫምባላላ በዓል ዋዜማ የሆነው የፊቼ (ፊጣራ) በዓል በትላንትናው ዕለት በሲዳማ ባህል አዳራሽ በድምቀት ተከብሮ የዋለ ሲሆን የጫምበላላ በዓልም በዛሬው ዕለት የክልሉ እና የፌዴራል የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል።

በማይዳሰስ ቅርስነት በዩኔስኮ በተመዘገበው በዚሁ በዓል ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሲዳማ ክልል እና የአጎራባች አካባቢዎች ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው።

በበዓሉ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጀላ መርዳሳ፣ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ናሲሴ ጫሊ፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

የፊቼ ጨምባላላ በዓል በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ላለፉት ሁለት ዓመታት በአደባባይ ሳይከበር መቆየቱ የሚታወስ ነው።

በኃይሉ ጌታቸው (ከሀዋሳ)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW