የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለህዳሴ ግድብ የ20 ሚሊየን ብር ቦንድ ግዥ ፈጸመ

መስከረም 27/2014 (ዋልታ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲውል የ20 ሚሊየን ብር ቦንድ ግዥ ፈጸመ።

የቦንድ ግዥ ድጋፉን የግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) ተረክበዋል።

ዳይሬክተሩ ኮርፖሬሽኑ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ባላቸው አቅም ሁሉ እያደረጉ ያለውን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

የቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል በበኩላቸው፣ ተቋሙ አገራዊ ፕሮጀክት ለሆነው የሕዳሴ ግድብ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ኢዜአ አንደዘገበው ተቋሙ ባለፈው ዓመትም የ20 ሚሊየን ብር ቦንድ ግዥ መፈጸሙን አውስተዋል።

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም ከ80 በመቶ በላይ መድረሱም ይታወቃል፡፡