መስከረም 20/2015 (ዋልታ) የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለመላ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ለ2015 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል የእንኳን በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
የኢሬቻ በዓል የክረምቱ ወራት አልፎና የውሃው ሙላት ጎድሎ ጥርት ብሎ የሚወርድበት፣ ጎርፉ ሰክኖ የሚጠራበት፣ ውሽንፍሩና ቁሩ ጠፍቶ በውብና በብሩህ ብርሀን የሚደምቅበት፣ አዝመራው የሚያሸትበት፣ እንስሳት የሚቦርቁበት አእዋፍ የሚዘምሩበት በመሆኑ ይህን ሁሉ ላደረገ ፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት በዓል ነው መሆኑን ምክር ቤቱ ገልጿል።
ምክር ቤቱ የኢሬቻ በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የወንድማማችነትና የአብሮነት በዓል እንዲሆንም ምኞቱን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስፍሯል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW