የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ለጠ/ሚ ዐቢይ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

ጥቅምት 5/2014 (ዋልታ) የፍልስጤም ራስ ገዝ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሃሙድ አባስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ድጋሚ በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ፕሬዝዳንት ሙሃሙድ አባስ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት የለዉጥ እና የብልፅግና እንዲሆን መልካም ምኞታቸዉን መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡