የፍትህ ሚኒስቴር አመራሮች ሃብት ተመዘገበ

መጋቢት 9/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የበላይ አመራሮች የሃብት ምዝገባ ተደረገ፡፡

የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ሙስናን ለመዋጋት ዲጂታል በሆነ መልኩ የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች የገቢ ምንጫቸው መታወቅ አለበት ብለዋል፡፡

በዚህም በአዲሱ የዲጂታል አሰራር የሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ሃብታቸውን ማስመዝገብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወዶ አጦ በአገሪቷ ከፍተኛ የሆነ የሙስና መስፋፋት በመስተዋሉ ይህን ለማስቀረት የጋራ ሥራ ያስፈልጋል  ብለዋል፡፡

ሙስናን ለመዋጋት የመንግሥት አገልግሎት ግልፅ እና ተጠያቂነት የሚታይበት መሆን እንዳለበትም አስረድተዋል፡፡

በሚልኪያስ አዱኛ