የፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ነፃ የአየር ሰአት ድልድል ለ12 ቀናት ተራዘመ

ግንቦት 21/2013 (ዋልታ) – የድምፅ መስጫ ቀን መራዘሙን ተከተሎ የፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ነፃ የመገናና ብዙሀን የአየር ሰአት ድልድል ለተጨማሪ 12 ቀናት ተራዘመ፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ  ሰጥተዋል፡፡

በዚህም ፓርቲዎች ነፃ የመገናኛ ብዙሀን የአየር ሰአታቸውን ተጠቅመው እስከ ሰኔ ዘጠኝ ድረስ መቀስቀስ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

የድምፅ መስጫ ቀን አራት ቀን እስኪቀረው ድረስ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ የሚካሄድ ሲሆን አራቱ ቀናቶች የፅሞናን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ነው ተብሏል::

(በመስከረም ቸርነት)