የፕላንና ልማት ሚኒስትር ከቱርክ ልማት እና ትብብር ኤጀንሲ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

ጥቅምት 24/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከቱርክ ልማት እና ትብብር ኤጀንሲ ኃላፊዎች ጋር በልማት ድጋፎች ላይ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሯ በውይይታቸው ለቱርክ የልማት እና ትብብር ኤጀንሲ ኃላፊዎች ኢትዮጵያ በልማት እቅዷ ቅድሚያ የምትሰጣቸውን ጉዳዮች አስረድተዋል።

ቱርክ የኢትዮጵያ የልማት አጋር እንደሆነች ያነሱት ሚኒስትሯ በትምህርት እና ተዛማጅ ጉዳዮች ያላትን አስተዋጽኦ አንስተው አገራቱ ያላቸው ቁርኝት አብራርተዋል።

የሁለቱ አገራት አጋርነት አሁን ካለው ጎልብቶ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት በማንሳትም በሁለቱም አገራት በኩል መደረግ ስለሚኖርባቸው ጉዳዮች ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።