የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ዓለም የኢትዮጵያን እውነታ መረዳት ይኖርበታል አሉ

ኅዳር 9/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያን ፈተናዎች አቅልለን አንመለከትም ነገር ግን ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ እውነታውን መረዳት ይኖርበታል ሲሉ የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ምዕራባዊያን የኋላ ታሪክን በአግባቡ በመረዳት የአፍሪካዊያንን በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያን አቅም ማመን አለባቸው ብለዋል፡፡

የሚደርሱብንን ትንኮሳዎች፣ ችግሮችና ማሰሪያ ማዕቀቦች እያሸነፍን ነፃነታችንን እናረጋግጣለን ሲሉም በቲዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡