የፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአዲስ ዓመት ስጦታ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ጳጉሜ 03/2013 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት በመከበር ላይ ባለው “የመልካምነት ቀን” በማስመልከት በአራዳ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የበዓል ስጦታ አበርክተዋል።

በድጋፍ መርኃግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ፕሬዘዳንት ሳህለ ወርቅ ሁላችንም እርስ በእርሳችን በመረዳዳት ወገኖቻችንን ልንደግፍ ይገባል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።