የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ማብራሪያ እየሰጠ ነው

ሐምሌ 30/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በአዲስ አበባ ማብራሪያ እየሰጠ ይገኛል።

በመድረኩ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ አምባሳደሮች እና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ ማብራሪያ በዋናነት አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሃገርና በሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን በደል ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ የሚያሳውቅበት መሆኑን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።