የ11ዱ አገራዊ የምክክር ኮሚሽነሮች ሹመት ፀደቀ

የካቲት 14/2014 (ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11 ኮሚሽነሮችን ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽነርነት ሾመ።

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮቸን ሹመት በ5 ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ አጽድቋል።

በዚህ መሰረት፡-
1. መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) (ሰብሳቢ)2. ሂሩት ገብረሥላሴ (ምክትል ሰብሳቢ)
3. ተገኘወርቅ ጌቱ (ዶ/ር)
4. አምባሳደር አይሮሪት መሃመድ (ዶ/ር)
5. ብሌን ገብረመድኅን
6. ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)
7. ዘገየ አስፋው
8. መላኩ ወልደማሪያም
9. አምባሳደር መሃሙድ ድሪር
10. ሙሉጌታ አጎ እና
11. አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን ወድ ብሔራዊ መግባባት ያመጣል የሚል እምነት የተጣለበት የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ሆነው ተሹመዋል።

ኮሚሽኑ ብሔራዊ መግባባትን ለማምጣት የሚያግዙ አጀንዳዎችንና የውይይት መድረኮችን በመቅረጽ ሰፊ ውይይቶችን የማካሄድ ኃላፊነት ተጥሎበታል