ሐምሌ 06/2013 (ዋልታ) – ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከጥቅምት 2014 ዓ.ም አጋማሽ በኋላ እንደሚሰጥ አስታወቀ።
በዘንድሮው የትምህርት ዘመን የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ሳይጨምር 620 ሺህ ተማሪዎች ተመዝግበው ፈተናውን በመጠባበቅ ላይ ናቸው ተብሏል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በሰጡት መግለጫ ኤጀንሲው በማንኛውም ሰዓት ፈተናውን መስጠት የሚያስችል ዝግጅት አድርጓል ብለዋል።
በሀገሪቱ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የኢኮኖሚክስ ትምህርት ባለመሰጠቱ ፈተናው የማይሰጥ እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።