የ2014 የውሃ ዋና ሻምፒዮና ተጀመረ

ሚያዝያ 1/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ስፖርቶች ፌዴሬሽን ያዘጋጀው የ2014 የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ሻምፒዮና በቢሾፍቱ ከተማ ተጀመረ።
በቢሾፍቱ ከተማ መኮንኖች ክበብ በጀመረው በዚህ ውድድር የአማራ፣ የጋምቤላ እና የሲዳማ ክልሎች ተሳታፊ ሲሆኑ የድሬዳዋ ከተማ እና የቢሾፍቱ ከተማ ተወዳዳሪዎችም ተገኝተዋል።
በክለብ ደረጃ ዳዊት እምሩ ህንፃ ተቋራጭ፣ ሳምሶን ውሃ ዋና ስፖርት ክለብ እና ኦሮሚያ ፖሊስ ተሳታፊ ሲሆኑ አቻላ ያኮቤ በግል ተወዳዳሪ በመሆን ቀርቧል።
ለአንድ ሳምንት በሚቆየው ውድድር መክፈቻ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር እንዲሁም የውሃ ዋና ስፖርቶች ፌዴሬሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በዚህም በሁለቱም ፆታ በተለያዩ ዘርፎች ስምንት የማጣሪያ እና የፍጻሜ ውድድሮች ተከናውኗል።
ደግነት መኩሪያ (ከቢሾፍቱ)