የ2017 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ

ጥቅምት 14/2017 (አዲስ ዋልታ) የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባቸውን መግለጫው ከወጣበት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ገልጿል።

በዚህም ተማሪዎች ተቋሞቹ በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት ምዝገባቸውን እንዲያካሂዱ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

በተጨማሪም ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑንም በመግለጫው አመላክቷል።

ተማሪዎች የተመደቡበትን የትምህርት ተቋም ለማወቅ https://placement.ethernet.edu.et እና https://t.me/moestudentbot መጠቀም እንደሚችሉ ጠቁሟል።